Madda Walabu University crest
Madda Walabu
University · Est. 2005
ገቢ ማመንጫ ሥራዎቻችን የተግባር ትምህርቱን እያገዙ ነው

ገቢ ማመንጫ ሥራዎቻችን የተግባር ትምህርቱን እያገዙ ነው

May 21, 2026

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ሆነው የውስጥ ገቢውን ሊያሳድጉ የሚችሉ ተጓዳኝ ሥራዎችን የዕቅዱ አካል አድርጎ እየሠራ ይገኛል።

ከነዚህም ምርጥ ዘር የማላመድና የማባዛት ሥራ ፣ የዶሮ እርባታ፣ የሆስፒታል አገልግሎት እና ከብቶችን የማድለብና ለገበያ ማቅረብ እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው። 

በተለይ በሀብት ልማት ገቢ ማመንጫ የሥራ ሂደት ከብቶችን በማድለብ ለገበያ የማቅረቡ ሥራን ለሁለተኛ ጊዜ ለፋሲካ በኃል ማድረስ ተችሏል ። 

በዚህም የውስጥ ገቢ ከማሳደግ ጎን ለጎን ዩኒቨርሲቲው የሚሰራቸውን የገቢ ማመንጫ ሥራዎች ከትኩረት አቅጣጫዎቹ ጋር (ማለትም ከግብርና ፣ ቱሪዝም ፣ ብዝሀ-ህይወት እና ከጤና) በማስተሳሰር ተማሪዎች በግቢያቸው ውስጥ በቅርበት በመስክ የተግባር ትምህርት የሚያገኙበት መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል።


#መወዩ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት

Related Articles

View All