Madda Walabu University crest
Madda Walabu
University · Est. 2005
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የምስለ-ችሎት (Moot Court) የፍፃሜ ውድድር ተካሄደ፡፡

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የምስለ-ችሎት (Moot Court) የፍፃሜ ውድድር ተካሄደ፡፡

May 21, 2026

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የምስለ-ችሎት የፍጻሜ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ። 

ውድድሩ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚያገኙትን ንድፈ-ሀሳብ እውቀት ከተግባራዊ ልምድ ጋር በማዋሃድ የሚያበረታታ መሆኑ ተገልጿል። በውድድሩ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሕግ ትምህርት ቤት ዲን መምህር ረሺድ ሐሰን ሲሆኑ፤ ተማሪዎች በዚህ ዓይነት የተግባር ስልጠና ላይ መሳተፋቸው በሙያዊ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ሹቤ በማክፈቻ ንግግራቸው ተማሪዎች በንድፈ-ሀሳብ ትምህርት ብቻ ሳይቀር እንደዚህ ያሉ ተግባራዊ ልምዶች ላይ መሳተፍ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው፤ መርሃ ግብሩ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።


በምስለ-ችሎቱ ላይ የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ የባሌ ዞን አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የሮቤ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በክብር እንግድነት የተነኙ ሲሆን ለሕግ ተማሪዎች የስራና ሕይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል።

በውድድሩም ተወዳዳሪ ተማሪዎች በተዘጋጀላቸው ንድፈ-ሀሳብ (hypothesis) ላይ በሁለት ቡድን ከሳሽ እና ተከሳሽ ተከፍለው ለ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ያህል የቆየ ክርክር አካሄደዋል። 

በዳኞች የተሰጠው ውጤት መሠረት የከሳሾች ቡድን 96 ነጥብ በማግኘት ክርክሩን በበላይነት ሲያጠናቅቁ፤ የተከሳሽ ቡድን 93 ነጥብ በማግኘት ጥሩ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል።

አሸናፊ የሆኑት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ወክለው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል በሚካሄዱ የምስለ-ችሎት ውድድሮች ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል። በመጨረሻም ውድድሩ ለተሳታፊዎች የእውቅና ሰርቲፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል፡፡


#መጋቢት 24/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ


Related Articles

View All