በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በአይነቱ ልዩ የሆነው ሀገር አቀፍ የአርሶ አደሮች የምርምር ኮንፍረንስ ‘’From Local Practices to National Impact: Recognizing Farmers as Innovators’’ በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የምርምር ኮንፍረንስ ተጠናቀቀ፡፡
ኮንፍረንሱ በሁለተኛው ቀን ውሎ የግብርና ግብአቶች ኤግዚቢሽን (Agricultural Exhibition) የተከፈተው በተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሲሆን በርካታ የግብርና ውጤቶች እና የግብርና ግብአቶች በኤግዝቢሽኑ ቀርበው ከተለያዩ ቦታ በመጡ እንግዶች፣ በተመራማሪዎች፣በአርሶ አደሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተጎብኝተዋል፡፡
በዚህ ሀገር አቀፍ በሆነው የአርሶ አደሮች የምርምር ኮንፍረንስ ላይ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከ15 በላይ ድርጅቶች በምርምር ያገኝዋቸውን የተለያዩ የግብርና ውጤቶች፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደጊያ ግብአቶች፣ የግብርናን ስራ የሚያቀሉ የምርምር ውጤቶች በስፋት ቀርበው ልምድ ተወስዶባቸዋል፡፡አርሶ አደሮችም ሆኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ከኤግዚቢሽኑ በእጅጉ ተጠቃሚ እንደሆኑ መረዳት ተችሏል፡፡
በመጨረሻም የሁለት ቀን ውሎ ማጠቃለያ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ እና በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የገጠር ልማት ፖሊሲ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ መገርሳ ገቢሳ መሪነት ከተሳታፊዎች ሀሳብና ጥያቄዎች በመቀበል ማብራሪያ ተሰቶበታል፡፡በቀጣይም ይህ አይነቱ ኮንፍረንስ የበለጠ ሰፍቶና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግባባት ኮንፍረንሱ ተጠናቋል፡፡
# ባሌ-ሮቤ ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ





