Madda Walabu University crest
Madda Walabu
University · Est. 2005
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በጡት ፣በጉሮሮ እና በጨጓራ ካንሰር ላይ ትኩረቱን ያደረገ የባለድርሻ አካላት ፓናል ውይይት ተደረገ

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በጡት ፣በጉሮሮ እና በጨጓራ ካንሰር ላይ ትኩረቱን ያደረገ የባለድርሻ አካላት ፓናል ውይይት ተደረገ

May 21, 2026

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በጡት ፣በጉሮሮ እና በጨጓራ ካንሰር ላይ ትኩረቱን ያደረገ “Enhancing Cancer awareness and Breast self-examination /BSE/,Bale zone south east Ethiopia Attention to Esophageal, Breast and Gastric cancer” በሚል የፕሮጀክት ስራ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ነው የፓናል ውይይት የተካሄደው፡፡

ይህ በጡት ፣በጉሮሮ እና በጨጓራ ካንሰርን ላይ ትኩረቱን ያደረገ የሶስት አመት ፕሮጀክት ሲሆን ስለበሽታው መንስኤ፣ምልክቶች ፣ቅድመ ጥንቃቄ መከላከያ መንገዶች እንዲሁም ምልክቱ በሚታይበት ወቅት ሰለህክምና አሰጣጥ ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፕሮጀክት ነው፡፡ፕሮጀክቱ ከጎባ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራር ሆስፒታል በተውጣጡ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ሰባት (7) ባለሙያዎች የሚሰራ ነው፡፡ 


በፓናል ውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ እና ልዩ አማካሪ አቶ ሌንጮ ሳሙኤል እንዳሉት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሶስት ዋና ዋና ተልእኮዎችን መማር ማስተማር፣ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማሀበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንዳለ አንስተው በምርምር ረገድ ዩኒቨርሲቲው ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት በአንድ አመት ይጠናቀቁ የነበሩ እና የተበጣጠሱ የምርምር አሰራሮችን በማስቀረት ከተለያዩ መስኮች በተውጣጡ ተመራማሪዎች በቅንጅት ተፅእኖ ፈጣሪ ፣ጠቃሚ እና ችግር ፈች የሆኑ የምርምር እና የፕሮጀክት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡አክለውም ይህ ከማህበረሰብ አገልግሎት ጋር የተገናኘ ፕሮጀክት ውይይት ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ ቦታ የመጣችሁ ባለድርሻ አካላት ከፓናል ውይይቱ ጥሩ ግንዛቤን በመውሰድ እና በጋራ በመስራት የማህበረሰቡን ችግር መፈታት እንዲቻል የበኩላቸውን አስተዋፅፆ እንዲያደርጉ አደራብለዋል፡፡

በመቀጠልም ዶ/ር ምትኩ ቦንሳ፣ዶ/ር ሙደስር አማን እና ዶ/ር አዲስ ጉልላት የሶስቱን የካንሰር አይነቶች፣ የችግሩን ስፋት፣የበሽታዎቹ መንስኤዎች፣ መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ፣የባለድርሻ አካላት ሚና እንዲሁም የፕሮጀክቱን አጠቃላይ አካሄድ አስመልክቶ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በውይይቱ ላይ የተገኙትም ባለድርሻ አካላት በራሳቸው እቅድ ውስጥ በማስገባት እና ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመሆን የበከላቸውን ሁሉ እንደሚወጡ አስረድተዋል፡፡


በመጨረሻም የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራር ሆስፒታል ኤክስኪዊቲቨ ዳይሬክተር የሆኑት መሀመድ አማን ማማ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የፓናል ውይይቱ እጅግ ጠቃሚ ሀሳቦች የተነሱበትና ኮሌጁ ባለው አቅም ሁሉ ከተመራማሪዎቹ እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡


# ባሌ-ሮቤ ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ

Related Articles

View All