Madda Walabu University crest
Madda Walabu
University · Est. 2005
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ለተለያዩ የስራ ክፍሎች ስልጠና ሰጠ

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ለተለያዩ የስራ ክፍሎች ስልጠና ሰጠ

May 21, 2026

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ለተማሪዎች ምግብ ቤት እና መኝታ ቤት ሠራተኞች ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳ ሐሰን፤ ዩኒቨርስቲው የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሻሻልና ለማዘመን በቀጥታ ከተማሪዎች ጋር ግንኙነት ላላቸው ክፍሎች ስልጠና መሰጠቱ አግባብነት እንዳለው ጠቅሰው፣ መሰል ስልጠናዎች በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እና ከስጋት ነፃ እንዲሆን የማድረግ ዓላማን ያነገበ እንደሆነም ገልፀዋል።


ስልጠናው በግል ንፅህና አያያዝ እና የአከባቢ ንፅህና አጠበበቅ፤ የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች አሰጣጥ እና አጠቃቀም፤ እንዲሁም የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 1353/2017 ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።

የግል ንፅህና አያያዝ እና የአከባቢ ንፅህና አጠባበቅ የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ክሊኒክ የህክምና ባለሙያ አቶ ጌታቸው ከተማ እና አቶ ስዩም አስቻለው የሰጡ ሲሆን የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ ቁሳቁስ አሰጣጥ እና አጠቃቀም ዙሪያ ወ/ሮ ወይንሸት አልታየ እንዲሁም በፌዴራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 1353/2017 ላይ ወ/ሪት ቤተልሔም ፍርዱ ስልጠናውን ሰተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች የተማሪዎች ምግብ ቤት እና መኝታ ቤት ሠራተኞች በጠቅላይ 430 በላይ ናቸው።

በተሰጠው ስልጠና ላይ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን፤ የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ የብቃት እና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ ከተማ መኮንን፤ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።


የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳ ሐሰን በበኩላቸው የምግብ ቤት እና መኝታ ቤት ሠራተኞች ወሳኝ የስራ ክፍሎች አንዱ ስለሆነ የተሰጠው ስልጠና የአገልግሎት አሰጣጥ እና ጥራቱን ይበልጥ ለማዘመን ወሰኝ መሆኑን አንስተው፤ መሰል ስልጠና በቀጣይነት እንደሚኖረውም ተናግረዋል።


# ባሌ ሮቤ ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ

Related Articles

View All